የ C.A.F.É Practice ስልጠና ተሰጠ፡፡

ድርጅታችን ለአረቢካ ቡና ምርቱ አስተማማኝ እና ቀጣይነት ያለው ዓለም አቀፍ ግብይት መፍጠር ያለውን ጠቀሜታ በመገንዘብ በዘርፉ መልካም ስም እና ከፍተኛ ልምድ ያለው ዓለም አቀፍ ኩባንያ ሲፈልግ ቆይቷል። በዚህ ረገድ በዓለም ትልቁ የቡና ግብይት ሰንሰለት ካለው ስታርባክስ ከተባለ የአሜሪካ ኩባንያ ጋር ጥሩ የንግድ ግንኙነት በመመስረት የቡና ሽያጭ ስራችንን ለማቀናጀት ታስቧል፡፡

ለዚህም የገበያ ቅንጅት የቅድመ ሁኔታ አካል የሆነውን ሰርቲፊኬት ለማውጣት እንቅስቃሴ ጀምረናል፡፡ ከመስፈርቶቹ አንዱ የሚመለከታቸው ሀላፊዎችና ባለሙያዎች ስልጠና ማግኘት በመሆኑ ስልጠናውን ለሚመለከታቸው መስጠት ተችሏል፡፡ 

this is edit

በስታር ባክስ የኢትዮጵያ ቢሮ ሕዳር 4 ቀን 2016 ዓ.ም ቃሊቲ በሚገኘው የድርጅታችን ቡና ማደራጃና ማዘጋጃ ማዕከል በተሰጠው ስልጠና በ C.A.F.É Practice መሰረታዊ ጽንሰ ሀሳቦች ዙሪያ የሚመለከታቸው ሁሉ ስልጠናውን ያገኙ ሲሆን በአጭር ጊዜ የምስክር ወረቀቱን በማግኘት የቡና ንግዱን ከስታር ባክስ ጋር ለማቀናጀት እንደሚያስችል ታምኖበታል፡፡

አስተያየት ይስጡ

Your email address will not be published. Required fields are marked *

amአማርኛ