ኮከብ ግራናይት

ለማንኛውን ጥያቄዎ!

በአድራሻዎቻችን ያግኙን

በኢንዱስትሪ ዘርፉ በዘመናዊ የቴክኖሎጂ ጥበብ የተመሰረተ የማምረቻ ፋብሪካ ሲሆን በአማራ ክልል ባህርዳር ከተማ ይገኛል፡፡ ከማዕድን ማውጫ ሳይት የሚመጡትን የተለያየ ቀለምና ቅርጽ ያላቸው የግራናይት አይነቶችን ወደ ፋብሪካችን በመላክ በደንበኞች ፍላጐት መሰረት እያቀረብን ሲሆን በከፍተኛ መጠን፣ ፍጥነትና ጥራት የማምረት አቅሙ የሚታወቀው ፋብሪካችን በአዲስ ቴክኖሎጂ ከፍተኛ ጥራት ያለውን ምርት በማምረት በተመጣጣኝ ዋጋ ምርቶቹን ለገበያ ያቀርባል፡፡

በሀገራችን የመጀመሪያ የሆነውን ቴክኖሎጂ ከጣሊያን ሀገር በማምጣት የተለያየ መጠንና ቅርጽ ያላቸውን የግራናይት ምርቶችን በደንበኞች ፍላጐት መሰረት እያመረትን ሲሆን ምርቶቻችን በተሻለ ጥራትና ውበት እንዲቀርቡ ኢፖክሲ ሬይዚን የተባለ ግብአትን በመጠቀም የደንበኞቻችንን ፍላጐት ለማርካት እየሰራን ነው፡፡ በኢትዮጵያ እያደገ ለመጣው የግንባታ ኢንዱስትሪ ፋብሪካችን የበኩሉን አስተዋፅኦ አድርጓል።

amአማርኛ