ኮከብ ቃና የምግብ ዘይት ማምረቻ

ለማንኛውን ጥያቄዎ!

በአድራሻዎቻችን ያግኙን

ኮከብ ቃና የምግብ ዘይት ማምረቻ

ኩባንያችን በምግብ ዘይት አቅርቦት የአገር ውስጥ አቅምን ለማሳደግና የውጭ ምንዛሬ እጥረትን ለመቅረፍ በማሰብ በኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት፣ በሸገር ከተማ፣ በቡራዩ ክፍለ ከተማ በሚገኘው የታጠቅ ኢንዱስትሪያል ዞን ውስጥ የምግብ ዘይት ማምረቻና ማቀነባበሪያ ፋብሪካ ሥራ ጀምሯል።

በተጨማሪም የማጣሪያ ቴክኖሎጂ ተከላ በማከናወን በቀን ከ 115 ቶን በላይ የምግብ ዘይት ለገበያ ለማቅረብ የሚያስችለውን አቅም ፈጥሯል።

ቤአኤካ ጠቅላላ ንግድ ስራ የአግሪ-ቢዝነስ ዘርፉን ከማኑፋክቸሪንግ ኢንዱስትሪ ጋር ለማስተሳሰር በሚያደርገው ጥረት በማጠናከር በአሁኑ ወቅት በአማራ ክልል ጃዊ በሚገኘው የተቀናጀ እርሻ ልማት ውስጥ ለዘይት ምርት የሚውሉ ግበአቶች (በተለይም አኩሪ አተር እና ሱፍ) በማምረት ላይ ይገኛል።

ISO 9001:2015, ISO 14001:2015 ISO 2200:2018 እና EIA ያሉ የቁጥጥር መስፈርቶችና ደረጃዎችን በማሟላትም የምርት ጥራትና የደንበኞችን እርካታን ለማሳደግ ጥረታችንን ቀጥለናል፡፡ 

amአማርኛ