ከባድ ተሽከርካሪዎች የመገጣጠም ስራ

ለማንኛውን ጥያቄዎ!

በአድራሻዎቻችን ያግኙን

ቤአኤካ ጠቅላላ ንግድ ስራ በሀገሪቱ ውስጥ ፈጣን የኢኮኖሚ እድገትን ማረጋገጥ በሚያስችሉ ዘርፎች በመሳተፍ ላበረከተው አስተዋጽኦ አንዱ ማሳያ በከባድ ተሽከርካሪ መገጣጠሚያ የተሰማራንበት ዘርፍ ነው፡፡ የከባድ ተሽከርካሪ መገጣጠሚያችን ወቅቱ ያፈራቸውን እጅግ ዘመናዊ ቴክኖሎጂዎች ተጠቅሞ ለተለያዩ ኢንዱስትሪዎች አገልግሎት መስጠት የሚችሉ የተለያዩ ተሽከርካሪዎችን በመገጣጠም ያቀርባል፡፡ ከባድ ተሽከርካሪዎችን በአገር ውስጥ በማምረት እና በመገጣጠም የሀገር ውስጥ ገበያን ፍላጐት ከማሟላት ባሻገር የውጭ ምንዛሬ እጥረትን ለመቅረፍ በሚያስችል መልኩ በሀገር ውስጥ ምርቶችን የማስፋፋት ስራ በሰፊው እየተሰራ ነው፡፡ የከባድ ተሽከርካሪ መገጣጠሚያ ፋብሪካችን ለበርካቶች የስራ ዕድል ከመፍጠሩ ባሻገር ቤአኤካ የሀገሪቱን ኢኮኖሚ ከፍ ለማድረግ የሚያበረክተው አስተዋጽኦ አንዱ ዘርፍ ሆኖ ይወሰዳል፡፡

amአማርኛ