ማህበራዊ ሃላፊነት

ማህበራዊ ኃላፊነታችንን ለመወጣት

የቤአኤካ ጥሩ የኮርፖሬት ማሕበራዊ ኃላፊነት (CSR) ተግባራት ሪከርድ ኩባንያው ታማኝነቱን፣ በአገር አቀፍ ደረጃ የምርት ስም ምስሎችን አትርፎለታል፣ እና በፕሮጀክቶቹ/የንግድ ስራዎቹ ዙሪያ ከአካባቢው ማህበረሰቦች ጋር እምነት እና አጋርነት ፈጥሯል።

ኩባንያችን ከተቋቋመበት ጊዜ ጀምሮ በተለያዩ አካባቢዎች ለተከሰቱ ችግሮች ለተጐጂዎች ድጋፉንና አጋርነቱ አላቋረጠም፣

  • ለጎርፍ እና የእሳት አደጋ ተጐጂዎች ፈጥነን ደርሰናል፣
  • ሰራተኞቻችን ደም እንዲለግሱ በማበረታታት እና በማስተባበር የሰው ልጅ ክቡር ህይወት በደም እጥረት እንዳይቀጠፍ የበኩላችንን አስተዋጽኦ አበርክተናል፣
  • ጤና ጣቢያዎችን፣ መንገዶችን፣ ፖሊስ ጣቢያዎችን ጥልቅ የውሃ ጉድጓዶችን በመቆፈር ህብረተሰቡ ማህበራዊ አገልግሎቶችን፣ ንፁህ የመጠጥ ውሀ በአቅራቢያው እንዲያገኝ በማድረጋችን ተጠቃሚዎች ምስጋናቸውን ችረውናል፣ብዙዎችን መጥቀም የቻሉ ት/ቤቶችን ገንብተን የማህበረሰብን እርካታ በማረጋገጣችን ደስተኞች ነን፣ ጥቂት ማሳያዎችን ብንመለከት፡-
    • በደብረ ማርቆስ ከተማ በሀዲስ አለማየሁ መታሰቢያ ትምህርት ቤት ያስገነባው 6 የመማሪያ ክፍሎች ያሎት ህንፃ፣
    • በጐደሬ ወረዳ ሜጢ ከተማ ለካቦ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት 3 ክፍል ያለው መማሪያ ብሎክ።
    • በፍኖተሰላም ከተማ ለአቅመ ደካሞች ገንብተን ያስረከብናቸው 12 መኖሪያ ቤቶች፣ 10 ኩሽናዎች እና 10 የሻወር አገልገሎት የሚሰጡ ክፍሎች ከብዙ በጥቂቱ ተጠቃሽ ናቸው፡

ድርጅታችን "ማህበራዊ እና አካባቢያዊ ጉዳዮችንከግምት ውስጥ የማያስገባ ኢንቨስትመንት አይኖረንም" የሚለውን መርህ በጥብቅ ይከተላል፡፡.

የተቀበልናቸው እውቅናዎች

amአማርኛ