በእሪል ስቴት ግንባታው ዘርፍ ህልምን ወደ እውነትነት የቀየረ ተግባርን በማከናወን የግንባታ ቡድናችንን፣ እጅግ ከፍተኛ ቴክኖሎጂ በመጠቀም የገነባናቸው ምስክሮች ሆነውናል፡፡ በግንባታዎቻችን ጥራት ያለው እቅድ ከማውጣት፣ ዲዛይን ከማድረግ እና ፕሮጀክቶችን ከማከናወን ጀምሮ በጥራት እስከሚጠናቀቁ ድረስ በልዩ ትኩረትና ክትትል መፈፀማቸውን እናረጋግጣለን፡፡
በባቡር መስመር ዝርጋታ በጥራትና በፍጥነት በማጠናቀቅ ልምዳችን እንታወቃለን፡፡ ይህ ብቻም ሳይሆን ተያያዥ የትራንስፖርት አውታሮችን በመገንባት በእውቀት እና በቴክኖሎጂ ታግዘን በጥራታቸው የታወቁ ግንባታዎችን እውን አድርገናል፡፡ ወደፊት ለሚኖሩ የባቡር መሠረተ ልማት ግንባታዎች ተመራጭ ሆነን ዘርፉን ለማሳደግ እንሰራለን፡፡
ለተጠረጉ የውሃ መስመሮች ከፍተኛ ደረጃ ያላቸውን የግንባታ አገልግሎቶቻችንን ይለማመዱ። የተዋጣለት ቡድናችን ቀልጣፋ የውሃ ማጓጓዣ መንገዶችን ለመፍጠር እጅግ በጣም ጥሩ ቴክኖሎጂን ይጠቀማል። ደንበኛን ማዕከል ባደረገ አቀራረብ ለጥራት፣ ለጥንካሬ እና በጊዜ ማጠናቀቅ ቅድሚያ እንሰጣለን። የውሃ ማጓጓዣ እይታዎን በፈጠራ እና በጥራት እንድናመጣ እመኑን።
ለረጅም ጊዜ የሚቆዩ እና አስተማማኝ የሆኑ የመንገድ እና አስፓልት ግንባታወችን በጥራትና በቅልጥፍና አጠናቀን እናስረክባለን፡፡ ለፕሮጀክቶቻችን ጥራትና ቅልጥፍና ትኩረት በመስጠት መሰረተ ልማቶቹ በላቀ ቴክኖሎጂ ተሰርተው ለአገልግሎት እንዲበቁ ሙሉ አቅማችንን ተጠቅመን እንሰራለን፡፡
ቤአኤካ በግንባታው ዘርፍ የካበተ ልምዱንና የጥራት መርሁን በመከተል በበርካታ የግንባታ ዘርፎች ላይ በስፋት ተሳትፏል፡፡ መኖሪያ አፓርትመንት፣ ኢንዱስትሪያል እና ሜጋ ፕሮጀክቶች በመገንባት ለዘርፉ እድገት አሻራውን እያሳረፈ የሚገኝ ሲሆን ጥራት ባለው መልኩ ግንባታዎችን በማከናወን፣ ዘመናዊ ማሽነሪዎችና የካበተ ልምድ ያላቸው ባለሙያዎቻችንን ተጠቅመን ከገነባናቸው ፕሮጀክቶች መካከል ፡-
ቤአኤካ ጠቅላላ ንግድ ስራ በከፍተኛ ጥራት መገንባት ያለባቸውን ፕሮጄክቶች ተረክቦ በሚፈለገው የጥራት ልክ ፈጽሞ ማጠናቀቅ የሚያስችለውን የቴክኖሎጅ አቅም ያካበተ ሲሆን ከፍተኛ ጥራት ያላቸውን የግንባታ ማሽነሪዎች በመጠቀም ስራውን እያከናወነ ይገኛል።