በላኪነት

ለማንኛውን ጥያቄዎ!

በአድራሻዎቻችን ያግኙን

በላኪነት

ድርጅታችን ቤአኤካ ጠቅላላ ንግድ ሥራ ኃ.የተ.የግ.ማህበር በዋናነት የግብርና ምርቶችን ወደ ተለያዩ የውጭ ሀገራት የሚልክ ሲሆን፤ ግብርና ለኢትዮጵያ መሰረታዊና ዋና የውጭ ምንዛሬ ማስገኛ ምንጭ ከመሆኑ አንፃር በትጋት የሚሰራበት ዘርፍ ነው፡፡

ድርጅታችን ጥራታቸውን የጠበቁና የደንበኞችን ፍላጎት ያሟሉ የቅባት እህሎች፣ ቡና፣ ጥራጥሬ እና የአኩሪ አተር ተረፈ ምርት (ከዘይት ፋብሪካችን የሚገኝ ምርት) በቀጥታ ለደንበኞቻችን እናቀርባለን። በላኪነት የንግድ ዘርፍ በፍጥነትና በስፋት በማደግ ላይ እንገኛለን፡፡ የወጪ ንግዳችን የተመሰረተባቸው ዋና ዋና መርሆዎች ጤናማ የንግድ ልምዶች እንዲሁም ለምርት እና አገልግሎት አሰጣጥ የላቀ ቁርጠኝነት ናቸው።

ምርታችንንም ከምንልክባቸው ሃገራት መካከል እንደ አውሮፓ፣ አሜሪካ፣ ሩቅ ምስራቅ፣ መካከለኛው ምስራቅ እና እስያ ሀገራት ያሉ የተለያዩ መዳረሻዎች ይገኙበታል። ያለንን ውጤታማነት መሰረት አድርገንም እንደገበያው ፍላጐት ወደ ሌሎች መዳረሻዎችም ምርቶችን መላክ በተመለከተ ከደንበኞች ጥያቄ ከቀረበ እናስተናግዳለን፡፡

ወደ ውጭ የምንልካቸው ዋና ዋና ምርቶች፡-

ቡና፡- በራሳችን የቡና እርሻ ኦርጋኒክ አረቢካ የ“ጎደሬ” ቡና በማምረት ለአለም አቀፍ ገበያ እናቀርባለን የምንልካቸው ዋና ዋና የቡና ዓይነቶች ጎደሬ፣ ሊሙ፣ ቴፒ፣ ቤንች ማጂ፣ ሲዳሞ፣ ጉጂ፣ ይርጋጨፌ እና ሌሎችም ናቸው። በተጨማሪም ከተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች ከተለያዩ የቡና አምራቾች ጋር በመቀናጀት አብረን እንሰራለን።

የቅባት እህሎች፡- ሰሊጥ (ሁመራ፣ ወለጋ እና ቀይ ሰሊጥ)፣ ኑግ፣ ጉሎ፣ ለውዝ...ወዘተ።

ጥራጥሬዎች፡- አኩሪ አተር፣ ሽንብራ (ዴሲ እና ካቡሊ)፣ ማሾ፣ ነጭ ቦሎቄ….ወዘተ፡፡  

የአኩሪ አተር ተረፈ ምርት (ከዘይት ፋብሪካችን የሚገኝ ምርት) እና በገዢዎች ጥያቄ መሰረት ሌሎች ምርቶችንም እንልካለን፡፡

ኩባንያው የራሱ 2 እርጥብ ወፍጮዎች ፣ አንድ ደረቅ ወፍጮ እና መጋዘኖች ያሉት ሲሆን ለአካባቢ ስነምህዳር ተስማሚ እንዲሆኑ ተደርገው የተተከሉ ናቸው።

በተጨማሪም ድርጅታችን በአዲስ አበባ ታጠቅ ኢንዱስትሪ አካባቢ የቅባት እህሎች እና ጥራጥሬዎች ማበጠሪያ ፋብሪካ፣ በሰዓት 5 ቶን የማቀነባበር አቅም ያለው የቡና ማቀነባበሪያና ማከማቻ ከነሙሉ የላብራቶሪ መለዋወጫዎች አሉት።

"በጊዜው ስለማድረስ አይጨነቁ!" 

ድርጅታችን የቅባት እህሎች እና ቅመማ ቅመም አዘጋጅቶ ላኪዎች ማህበር (ኤፖስፒያ)፣ የኢትዮጵያ የንግድና የዘርፍ ማህበራት ምክር ቤት፣ የኢትዮጵያ ምርት ገበያ ECX፣ የኢትዮጵያ ጥራጥሬ፣ እና የኢትዮጵያ ቡና ሳይንስ ማህበረሰብ አባል ነን።

ግልጽ እና ማራኪ ምስል በአለም አቀፍ ገበያ ላይ ትልቅ ነጥብ እንደመሆኑ መጠን የመጋዘኑ/የእርሻ ቦታው/ምርቱ….ምስሎች በየጊዜው ከፍተኛ ጥራት ባለው ካሜራ ምርት የሚገኝበትን ቦታ በትክክል መውሰድ አለበት።

amአማርኛ