SHACMAN Heavy Duty Trucks

ለማንኛውን ጥያቄዎ!

በአድራሻዎቻችን ያግኙን

ሻክማን ከባድ ተሽከርካሪዎችን

ድርጅታችን ቤአኤካ ጠቅላላ ንግድ ስራ ኃ.የተ.የግ.ማህበር የSHACMAN ብራንድ X3000 ሞዴል የጭነት ተሽከርሪዎችን እና ኦሪጅናል መለዋወጫዎቻቸውን በኢትዮጵያ እና ጅቡቲ አስመጪ እና አከፋፋይ ነው

ቤአኤካ የተለያዩ የሻክማን ብራንድ ተሽከርካሪ ሞዴሎችን ለመገጣጠም የሚያስችለውን ፋብሪካ በድሬዳዋ በመገንባት ላይ ሲሆን፤ በተጨማሪም በዘመናዊ ቴክኖሎጂና ግብአት በተሟላውና አዲስ አበባ፣ ሃና ማርያም በሚገኘው ወርክሾፕ አስተማማኝ የጥገና አገልግሎት ለመስጠት የሚያስችለውን አቅም አደራጅቷል፡፡

በምርት ጥራት፣ አስተማማኝነት፣ ደህንነት፣ በተመጣጣኝ ዋጋ እና በድህረ ሽያጭ ወቅት በምንሰጠው የጥገናና የማማከር አገልግሎት በርካታ የመንግስት እና መንግስታዊ ያልሆኑ ደንበኞቻችን ዋና ምርጫቸው አድርገውናል፡፡

ሻክማን ከባድ ተሽከርካሪዎችን በማምረት ዘርፍ ከግማሽ ምዕተ ዓመት በላይ ልምድ ያለው፣ በኢስያ አህጉር ግዙፍ የተሸከርካሪ አምራች ሲሆን በምርት ጥራቱ ዓለም አቀፍ ደረጃውን የጠበቀ፣ በስፋት በማምረት የታወቀና ዘመናዊ ቴክኖሎጂን የታጠቀ የቻይና ኩባንያ ነው፡፡

በአሁኑ ወቅት እነዚህ ታዋቂ ከባድ ተሽከርካሪዎች ከ90 በላይ በሚሆኑ ሀገራት ላይ ለገበያ የቀረቡ ሲሆን የተፈበረኩበት ዘመናዊ ቴክኖሎጂ፣ በተለያዩ መልክአ ምድርና በብቃት አገልግሎት የሚሰጡ በመሆናቸው በኢንዱስትሪው ግንባር ቀደም ቦታን ይዘው ይገኛሉ። ሻክማን በአፍሪካ፣ መካከለኛው ምስራቅ፣ ደቡብ ምስራቅ እስያ፣ መካከለኛው፣ ደቡብ አሜሪካን እና ምስራቅ አውሮፓን በሚያጠቀልል ሁኔታ የግብይቱ ተደራሽነት በማስፋት የሚገኝ ኩባንያ ነው፡፡

ሻክማን ለጭነት መኪናዎቹ የሚከተሉትን አምስት ዋና ዋና የምርት ቴክኖሎጂዎችን ይጠቀማል።
• Wei Chai Engine
• FAST Gearbox
• HANDE (MAN) and BPW Axle
• WABCO valves
• ZF steering technology, etc
ዋና ዋና ምርቶቻችን የሚከተሉት ናቸው፡-
የጭነት መኪናዎች
ተጎታች ያላቸው የጭነት መኪናዎች
ተጎታች ያላቸው የነዳጅ ጫኝ መኪኖች
ፓወር ትራክ
ገልባጭ መኪና
ሚክሰር ከባድ ተሽከርካሪ
እና ሌሎች ልዩ ተሽከርካሪዎች (እንደ የውሃ መጫኛ ቦቴ ተሽከርካሪ፣ የቆሻሻ ማንሻ፣ የፍሳሽ ማስወገጃ፣ የእሳት አደጋ መከላከያ፣ ክሬን እና ሌሎችንም ያመርታል፣ ያከፈፍላን ጥገና ያከናውናል፡፡

ለእያንዳንዱ ሞዴል መለዋወጫ ሙሉ በሙሉ በአገር ውስጥ በቤአኤካ የመለዋወጫ ማዕከላትና በችርቻሮ መሸጫዎች ይገኛሉ።

ለተጨማሪ መረጃ እና የምርት ዝርዝሮች እባክዎን ከዚህ በታች ያለውን ማስፈንጠሪያ ተጠቅመው የድርጅቱን ድረ-ገጽ ይጎብኙ። http://www.shacman.com.

amአማርኛ