ቡና ማጽዳት፣ ደረጃ መስጠት እና መጋዘን

ለማንኛውን ጥያቄዎ!

በአድራሻዎቻችን ያግኙን

ቡና ማዘጋጃና ደረጃ ማውጫ

ቡናን ለውጭ ገበያ የምናዘጋጅባቸው ማሽኖች በዋናነት አውሮፓ ሰራሽና ደረጃቸውን የጠበቁ ቴክኖሎጂዎች ሲሆኑ በተለይ ጀርመን ሰራት የሆኑት እነዚህ ማሽኖች በሰዓት 7.5 ቶን ቡና የማዘጋጀት አቅም ያላቸው ሲሆን በርካታ ቡና ላኪዎች እኛን በጽዳት፣ በፍጥነትና በምንጠቀመው ቴክኖሎጂ ዋናው ምርጫቸው እንድንሆን አድርጎናል፡፡ የማከማቻ ቦታችን አስተማማኝነት፣ ቅልጥፍናና ፍትሃዊ ዋጋ የተመራጭነታችን ሌሎች ምክንያቶች ናቸው፡፡

ቡና የማጽዳት ሂደታችን

ቃሊቲ ቡና ማቀነባበሪያና ማሸጊያ

ይህ ተቋም በአዲስ አበባ አቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ውስጥ የሚገኝ ሲሆን በኢትዮጵያ ምርት ገበያ ባለስልጣን በተቀመጠው ደረጃ መሰረት በሰዓት ከ5.78 ቶን በላይ የማምረት አቅም ያለው እጅግ ዘመናዊ ቴክኖሎጂ የተገጠመለትና ለውጭ ገበያ የሚውል የታጠበና የቅሽር ቡናዎችን በጥራት አዘጋጅቶ በማቅረብ ላይ ነው፡፡ 

ተቋሙ በዋነኛነት በጎደሬ ከሚገኘው የኩባንያው የቡና እርሻ ልማት ድርጅት ጋር ትስስር እንዲኖረው በኩባንያው ስር የተቋቋመ የአገልግሎት ዘርፍ ሲሆን አገልግሎቱን ከራሱ እርሻ ከሚመጣው የቡና ምርት ባሻገር ለእህት ኩባንያዎችና ለሌሎች የውጭ ደንበኞችም ጭምር በስፋትና በጥራት አገልግሎቱን እየሰጠ ይገኛል፡፡

amአማርኛ