ጥራጥሬና የቅባት እህሎች ምርት

ለማንኛውን ጥያቄዎ!

በአድራሻዎቻችን ያግኙን

ጃዊ የተቀናጀ ሜካናይዝድ እርሻ ልማት

በአማራ ክልል በአዊ ዞን በጃዊ ወረዳ 4ሺ ሄክታር መሬት የሚሸፍነው ይህ የተቀናጀ ሜካናይዝድ እርሻ ልማት የቅባት እህሎችን፣ ጥራጥሬዎችንና ሌሎች የብርዕና አገዳ ሰብሎችን እንዲሁም ፍራፍሬ ለማምረት ታስቦ ተግባራዊ እንቅስቃሴ እየተደረገ ይገኛል። እርሻ ልማቱ ከአዲስ አበባ 595 ኪ/ሜ፣ ከባህርዳር ደግሞ 270 ኪ/ሜ ርቀት ላይ ከባህር ጠለል በላይ 1100-1250 ሜ. በሆነ ከፍታ ላይ ይገኛል፡፡ የአካባቢው አማካይ የዝናብ መጠን 900-1100 ሚ.ሜ ፣ የሙቀት መጠኑ ደግሞ ከ17እስከ 32 ዲግሪ ሴልሽየስ ይሆናል፡፡ በአሁኑ ጊዜ እርሻው አኩሪ አተር፣ ሩዝ፣ በቆሎ እና ማሽላ ማምረት የሚችል ሲሆን በዓመት ሁለት ጊዜ ምርት መሰብሰብ ይቻል ዘንድ በቴክኖሎጂ የታገዘ የመስኖ ዘዴ በመጠቀም ስንዴ እና ማሾ በደረቅ ወራትም በማፈራረቅ ዘዴ እንዲመረቱ እየተደረገ ይገኛል። በመሆኑም ከእርሻው የሚመረተው የቅባት እህል ከሌሎች ከአካባቢው አርሶ አደሮች ጋር በኮንትራት እርሻ ከሚመረተው ጋር በማዳበል ኩባንያው በኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት፣ በሸገር ከተማ፣ በቡራዩ ክፍለ ከተማ በሚገኘው የታጠቅ ኢንዱስትሪያል ዞን ውስጥ ለሚገኘው የኩባንያው የምግብ ዘይት ማምረቻና ማቀነባበሪያ ፋብሪካ ዘላቂ እና አስተማማኝ የጥሬ ዕቃ አቅርቦትን ለማረጋገጥ የተቀናጀ እንቅስቃሴ የሚያደርግ የእርሻ ልማት ተቋም ነው፡፡

የቆታ እርሻ ልማት

የእርሻ ልማቱ በቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል፣ መተከል ዞን፣ ዳንጉር ወረዳ ቆታ ቀበሌ ውስጥ ይገኛል፡፡ ፕሮጀክቱ በ3,231 ሄክታር መሬት ላይ የተጀመረ ነው፡፡ አካባቢው ከባህር ጠለል በላይ ከፍታው ከ1,000-1,200 ሜትር፣ አማካይ የዝናብ መጠኑ 1,236-1,928 ሚሜ፣ አማካይ የሙቀት መጠኑ ከ16-32 ዲግሪ ሴልሺየስ ሲሆን ደረቅ ወይም ከፊል በረሃማ አካባቢ በሚባለው ስነ ምህዳር ውስጥ ይካተታል፡፡ ይህም የአየር ንብረቱ ዘመናዊ የሜካናይዜሽን ቴክኖሎጂዎችን በመጠቀም አኩሪ አተርና ሌሎች የቅባት፣ የሰብልና የጥራጥሬ ሰብሎችን ለማልማት ምቹ መሆኑን ያሳያል።

amአማርኛ