ስለ ግንባታ ስራዎቻችን

ለማንኛውን ጥያቄዎ!

በአድራሻዎቻችን ያግኙን

The Construction Business sector with the motto “Quality First ”

የኮንስትራክሽን ቢዝነስ ዘርፋችን "ቅድሚያ ለጥራት" በሚል መሪ ቃል ዘርፈ ብዙ የሆኑ ኢንደስትሪያል፣ መሰረተ ልማት እና ሪል ስቴት ፕሮጄክቶች ውስጥ በሰፊው እየተሳተፍንበት ያለ ሌላኛው የድርጅታችን ዘርፍ ነው፡፡ ኩባንያችን በአሁኑ ጊዜ በካፒታል እንዲሁም በግንባታ ልምዱ የካበተ በመሆኑ ደንበኞቻችን በሰጠናቸው ቀልጣፋና ጥራት ያለው አገልግሎት፣ በወቅቱ ባስረከብናቸው ፕሮጀክቶች፣ በተመጣጣኝ ዋጋ ላቀረብንላቸው አገልግሎት ምስጋናቸውን ችረውናል፡፡

አሁንም ጥራትን ተቀዳሚ በማድረግ፣ የበርካታ አመታት የግንባታ ልምዳችንን በመጠቀም ለግዙፍና ቴክኖሎጂን ብሎም ቅልጥፍናን ለሚጠይቁ ግንባታዎች ቀዳሚ ተመራጭ ሆነን እንቀጥላለን፡፡



የጥራት መገለጫዎቻችን

 ቤአኤካ ጠቅላላ ንግድ ስራ ጥራት ያለው ስራን በሰዓቱ ማድረስ ፣ የሙያዊ አገልግሎት እና ፕሮጅክት አስተዳደርን ጨምሮ በሁሉም የስራ ዘርፎች የደንበኞችን ፍላጎት ለማርካት ቁርጠኛ ነው።

ሁሉም የኩባንያው ሰራተኞች ለዚህ ፖሊሲያችን ተፈጻሚነት ይተጋሉ። ይህንን እቅዳችንን ተግባራዊ ለማድረግ በኩባንያችን ክትትልና ቀጣይነት ያለው ድጋፍ ይደረጋል፡፡ ሁሉም ባለሙያዎቻችን ከማህበረሰቡ ጋር በአግባቡና በቅርበት እየሰሩ በጥራትና በስርዓቱ ያልተከናወኑ ማናቸውም ችግር ሲኖር ለድርጅታችን ቀልጣፋ ሪፖርት ማደረረግ ሌላው መርህ ነው፡፡

ድርጅታችን በአሁኑ ወቅት ደረጃ-1 አጠቃላይ ተቋራጭ፣ /ውሃ ስራዎች፣ ኤሌክትሮ ሜካኒካል ስራዎች፣ ሪል እስቴት እና ኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ግንባታ ፈቃድ ያለው ድርጅት ነው፡፡

amአማርኛ