ቡናና ቅመማ ቅመም

ለማንኛውን ጥያቄዎ!

በአድራሻዎቻችን ያግኙን

ጎደሬ ቡናና ቅመማ ቅመም እርሻ ልማት

የጎደሬ ቡናና ቅመማ ቅመም እርሻ ልማታችን በሀገራችን የደቡብ ምዕራብ ክፍል በጋምቤላ ክልል በማጃንግ ዞን ጎደሬ ወረዳ ውስጥ የሚገኝ ሲሆን፣ አካባቢው ከባህር ጠለል በላይ ከ1,600 እስከ 2,100 ሜትር ከፍታ ባለው በትሮፒካል ሞቃታማ የአየር ንብረት የሚመደብ ሆኖ፣ የተፈጥሮ ደንና በርካታ ምንጮች እንዲሁም በዙሪያው በርካታ ዓመቱን ሙሉ የሚፈሱ ወንዞች ካሉበት ውብ የተፈጥሮ መስህብ በተጎናፀፈ ስፍራ ላይ የሚገኝ የእርሻ ልማት ነው፡፡

የእርሻ ልማቱ የሚገኝበት ስነ-ምህዳር ከሁለት የደረቅ ወራት በስተቀር ዓመቱን በሙሉ በሚባል ደረጃ ዝናብ የሚያገኝ አካባቢ ሲሆን የእርሻ ልማታችን አጠቃላይ ይዞታ 2,976 ሄክታር መሬትን ይሸፍናል፡፡ ሙሉ ለሙሉ ለዘመናዊ ቡና እና የቅመማ ቅመም ልማት የተመቸ፣ በተፈጥሮ ሀብት በበለፀገ ቦታ ከፍተኛ ጥራት ላለው የቡና እና የቅመማ ቅመም ምርት ተስማሚ በሆነው ቦታ ላይ ድርጅታችን ደረጃውን የጠበቀ የማሳ እንክብካቤ፣ የሰብል አያያዝና አመራረት ሂደትን በመተግበርና በዘመናዊ የቡና ማቀነባበሪያ ፋብሪካዎች በመጠቀም የቡና ልማት ስራውን ያከናውናል፡፡ ከፍተኛና ጥራት ያለው ምርት ለማግኘት ከሚያስችሉ ቴክኖሎጂዎች መካከል በሰዓት 12 ቶን መፈልፈል የሚችሉ የሁለት የእርጥብ ቡና ማቀነባበሪያ ፋብሪካዎችና ዘመናዊ ሰው ሰራሽ የቡና ማድረቂያ ማሽንም ባለቤት ሲሆን በተጓዳኝም በሰዓት 6 ቶን የማበጠር አቅም ያለው የደረቅ ቡና ማቀነባበሪያም አለው፡፡ የእርሻው አመቺ የተፈጥሮ አቀማመጥ፣ ለም አፈር እና የአካባቢ ስነ ምህዳር ተስማሚነት ዘመናዊ እና ከፍተኛ ጥራት ያለው ቡና እና ቅመማ ቅመም ለማምረት ጥሩ መሰረት ከመጣሉ ባሻገር ኩባንያው በቀጣይ ለሚሰራቸው ሌሎች መሰል ግብርና-ተኮር ፕሮጀክቶች አስተማማኝ ተሞክሮ ማበርከት ችሏል።

amአማርኛ