ከባድ ተሽከርካሪዎችን ለመገጣጠም ከሻክማን ጋር የተደረገው ስምምነት

  • Home
  • ከባድ ተሽከርካሪዎችን ለመገጣጠም ከሻክማን ጋር የተደረገው ስምምነት

ከባድ ተሽከርካሪዎችን ለመገጣጠም ከሻክማን ጋር የተደረገው ስምምነት

ድርጅታችን ቤአኤካ ጠቅላላ ንግድ ሥራ ኃ/የተ/የግል/ማህበር ለባለፉት ዓመታት በበርካታ የንግድ እና የልማት ሥራዎች ላይ በንቃት ሲሳተፍ የቆየ ግዙፍ ሀገር በቀል ኩባንያ ነው፡፡

በንግድ፣ በኢንዱስትሪ፣ በእርሻ፣ በኮንስትራክሽ እና በሪል እስቴት የሥራ ዘርፎች ላይ ከፍተኛ እንቅስቃሴ በማድረግ ለኢኮኖሚ እድገት ከፍተኛ አስተዋጽኦ ያበረከተና ሰፊ የሥራ እድል መፍጠር የቻለ ተቋም ለመሆን በቅቷል።

ከሻክማን ግሩፕ ጋር የተደረገው የከባድ መኪኖች መገጣጠሚያ ፋብሪካ ስምምነት ድርጅታችን በኢንዱስትሪው ዘርፍ ተሰማርቶ ከዚህ ቀደም የፈጠረውን ልምድ፣ እውቅና እና በጎ ስም አጠናክሮ የሚቀጥልበት ነው።

የትራንስፖርት ዘርፍ እድገት ለአንድ ሀገር ከፍተኛ የሆነ የኢኮኖሚ እንቅስቃሴን ለማስተሳሰር የሚያስችል መሰረታዊ ከመሆኑም ባሻገር የትራንስፖርት እና ሎጅስቲክስ አለማደግ በዋጋ ግሽበትና ምርታማነትን ላይ ያለው ተጽዕኖ ከፍተኛ ነው።

ድርጅታችን ይህንን በመረዳት በሃገራችን እየተስተዋለ ያለውን አሳሳቢ የሆነ የትራንስፖርት ክፍተት ለመሙላት፤ ከፍተኛ ጥራት፣ ረዘም ያለ ልምድ እንዲሁም ተመጣጣኝ ዋጋ ካለው የቻይና መንግስት ኩባንያ ከሆነው ከሻክማን ግሩፕ ጋር በመጣመር ከባድ ተሽከርካሪዎችን ገጣጥመን ለገበያ ለማቅረብ ዝግጅታችንን አጠናቀናል።

 

amአማርኛ