የውሃ ቁፋሮ እና ማጣሪያ ግንባታዎች

ለማንኛውን ጥያቄዎ!

በአድራሻዎቻችን ያግኙን

ቆሻሻ ውሃ ማጣሪያ ግንባታዎች

በድርጅታችን ቤአኤካ ጠቅላላ ንግድ፤ ግንባታ ዘርፍ ውስጥ ያለው የቆሻሻ ውሃ ማጣሪያ ግንባታ ክፍል የተለያየ ዓይነት ማጣሪያ ፓኬጆችን በመገንባት የካበተ ሙያ ያላቸው ኤክስፐርቶች የሰባሰቡበት ነው፡፡ ለኢንዱስትሪ እና ለማዘጋጃ ቤት አገልግሎት የቆሻሻ ማጣሪያ “MBR (membrane bioreactor), MBBR (moving bed biofilm reactor), and FBR (fixed bed reactor)” ማጣራትን ጨምሮ ለዘይት ማቀነባበሪያ ፋብሪካዎች ተብለው የተነደፉ አጣርቶ ማከሚያዎችን የመገንባት የካበተ ልምድ አለን።

ቤአኤካ በአሁኑ ጊዜ የከተሞች እና የኢንዱስትሪ ፍላጎቶችን ለማሟላት ይህንን ክፍል በማስፋፋት እና ትላልቅ ፕሮጀክቶችን በኢትዮጵያ ውስጥ በመውሰድ ላይ ይገኛል፡፡ እውቀታችን እና እያደገ የሚሄደው አቅማችን በእነዚህ ዘርፎች ውስጥ የቆሻሻ ውሃ አያያዝ ፍላጎቶችን ለማሟላት በእጅጉ ዝግጁ አድርጐናል።

የዉሃ ጉድጓድ ቁፋሮ

የውሃ ዲፓርትመንታችን ከቱርክ የገቡ አዳዲስ የቁፋሮ ማሽኖችን የያዘ፣ ልዩ የቁፋሮ ቡድን የተደራጀበት ሲሆን ማሽኖቻችን እስከ 800 ሜትር ጥልቀት መቆፈር የሚችሉ ናቸው። ከነዚህ የተራቀቁ ማሽነሪዎች ጋር፣ ሙሉ የሰለጠነ ባለሙያዎች እና ከፍተኛ ደረጃ ያላቸው መሳሪያዎች አሉን። በተለይ አስቸጋሪና ፈታኝ የሆኑ ቦታዎችን ለመቆፈር ከፍተኛ አቅም ያላቸው ናቸው፡፡ ከእነዚህም መካከል በተለያዩ የሀገሪቱ ክልሎች ለድርጅታችን ፕሮጀክቶች 12 እና ለቲ.ኤ.ቲ ኮንስትራክሽን 2ከፍተኛ ጥልቀት ያላቸውን ጉድጓዶች ቆፍረን ያስረከብን ሲሆን አሁንም የተለያዩ ሥራዎችን በማከናወን ላይ እንገኛለን፡፡

ከዋና ጥንካሬዎቻችን አንዱ ከገበያ ጋር ሲነጻጸር ተወዳዳሪ ዋጋ የማቅረብ ችሎታችን ነው። የአገልግሎቶቻችን ጥራት በማሳደግ ወጪ ቆጣቢ አገልግሎቶችን ለማቅረብ እንጥራለን። በቁፋሮው ዘርፍ ያለን ልምድ፣ ውጤታማ ፕሮጀክቶችን አጠናቆ በወቅቱ የማስረከብ ልምዳችን መልካም ስም እንዲኖረን አስችሎናል።

"ቅድሚያ ለጥራት"

amአማርኛ