Training on strategic performance and Leadership Development

ቤአኤካ ጠቅላላ ንግድ ሥራ ኃ/የተ/የግ/ ማህበር ለማኔጅመንት አባላትና የሥራ ክፍል ኃላፊዎች ሥልጠና ሰጠ።
አዲስ አበባ፣ ሕዳር 2/2017 (ቤአኤካ ሚዲያና ኮሙኒኬሽን)

ቤአኤካ ጠቅላላ ንግድ ሥራ ኃ/የተየግ/ ማህበር ለድርጅቱ የማኔጅመንት አባላትና የሥራ ክፍል ኃላፊዎች ሥልጠና ሰጥቷል።

ሥልጠናው የአመራሮችንና የፈፃሚዎችን አቅም በማሳደግ የድርጅቱን ውጤታማነት ከፍ እንደሚያደርግ ታምኖበታል።

ኢትዮ ኢምፓክት ከተባለ አማካሪ ድርጅት ጋር በመተባበር ከጥቅምት 30 እስከ ሕዳር 1/2017 ለ2 ቀናት በአዲስ አበባ ሞናርክ ሆቴል የተሰጠው ሥልጠና ፐርሰናል ዴቨሎፕመንት፣ ስትራቴጅክና ኦፕሬሽናል ሊደርሽፕ፣ ፐርፎርማንስ ማኔጅመንት የተሰኙ ርዕሰ ጉዳዮችን አካቷል።

በሥራ ላይ ውጤታማ እንዲሆኑ የሚያግዝ ሥልጠና ከመሆኑ በተጨማሪ የህይወት ልምድና ተሞክሮዎችን የተጋሩበት ቆይታ እንደነበር ሠልጣኞች ተናግረዋል።

የመዝጊያ ንግግር ያደረጉትና የሥራ መመሪያ የሰጡት የድርጅቱ ማኔጅንግ ዳይሬክተር አቶ ሚካኤል ካሳ በበኩላቸው ቤአኤካ ለያዘው የውጤታማነት ጉዞ የአመራርና የሠራተኞችን አቅም መገንባት ላይ በትኩረት እንደሚሰራ ተናግረዋል።

“አቅዶ አለመፈፀም አይቻልም!” ሲሉ በአፅንኦት የተናገሩት ማኔጅንግ ዳይሬክተሩ ለዚህ መርሀችን ስኬት ደግሞ በአዳዲስ አስተሳሰብ የተቃኜ፣ ለለውጥ የሚተጋና ችግር ፈቺ አመራር አስፈላጊ ነው ብለዋል።

ማኔጅንግ ዳይሬክተሩ ሥልጠናውን በጥራትና በተደራጀ አግባብ ላዘጋጀው ኢትዮ ኢምፓክት ኮንሰልቲንግና ለድርጅታችን የሰው ኃይል አስተዳደር ልማት መምሪያ ምስጋናቸውን ችረው ቀጣይ የሥራ መመሪያ በመስጠት ሥልጠናው ተጠናቋል።

አስተያየት ይስጡ

Your email address will not be published. Required fields are marked *

amአማርኛ