የቤአኤካ ጠቅላላ ንግድ ሥራ ኃላ/ የተ/ የግ/ ማኅበር አመራርና ሠራተኞች የአረንጓዴ አሻራ መርሀግብር አከናወኑ

  • Home
  • Uncategorized
  • የቤአኤካ ጠቅላላ ንግድ ሥራ ኃላ/ የተ/ የግ/ ማኅበር አመራርና ሠራተኞች የአረንጓዴ አሻራ መርሀግብር አከናወኑ

ቤአኤካ ጠቅላላ ንግድ ሥራ ኃላ/ የተ/ የግ/ ማኅበር አመራርና ሠራተኞች የአረንጓዴ አሻራ መርሀግብር አከናወኑ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 16፣ 2017 (ቤአኤካ ሚዲያና ኮሙኒኬሽን)

የቤአኤካ ጠቅላላ ንግድ ሥራ ኃላ/ የተ/ የግ/ ማኅበር አመራርና ሠራተኞች የአረንጓዴ አሻራ መርሀግብር ትናንት ሐምሌ 15/2017 ዓ.ም ተካሂዷል።

በመርሃግብሩ የድርጅቱ ማኔጅንግ ዳይሬክተር አቶ ሚካኤል ካሳ፣ የመምሪያ ዳይሬክተሮችና ሠራተኞች ተሳትፈዋል።

ማኔጅንግ ዳይሬክተሩ አቶ ሚካኤል ካሳ ቤአኤካ በየአመቱ በሚካሄደው የአረንጓዴ አሻራ መርሀ ግብርና የድርጅቱ ፕሮጀክቶችና ፋብሪካዎች ባሉባቸው አካባቢዎች የተለያዩ ችግኞችን በመትከልና በመንከባከብ ሀገራዊ ኃላፊነቱን እየተወጣ ይገኛል ብለዋል።

ከዚህም በተጨማሪ የበጎነት ተግባራት ላይ የድርጅቱን ተሳትፎዎች ያስታወሱት ማኔጅንግ ዳይሬክተሩ በቀሪ የክረምት ወራትና በመጭው አዲስ ዓመት መባቻ ወቅቶች በሚካሄዱ የማህበረሰብ አገልግሎትና የበጎ ፈቃድ ሥራዎች ላይ ሠራተኞች በንቃት እንዲሳተፉ ጥሪ አቅርበዋል።

***

በሁሉም መስክ ለአንደኝነት እንሠራለን!

አስተያየት ይስጡ

Your email address will not be published. Required fields are marked *

amአማርኛ