የድርጅቱ መገለጫ

ስለ ኩባንያችን፡-

ድርጅታችን ቤአኤካ ጠቅላላ ንግድ ስራ ኃላፊነቱ የተ.የግል ኩባንያ በኢትዮጵያ ፈጣን ዕድገት እያስመዘገቡ ካሉ የንግድ ድርጅቶች አንዱ ሲሆን በአሁኑ ወቅት በተለያዩ ዘርፎች ማለትም በማኑፋክቸሪንግ ኢንዱስትሪ፣ በማዕድን፣ በኮንስትራክሽን፣ በግብርና፣ በፔትሮሊየም ስርጭትና ንግድ እንዲሁም በአስመጪ እና ላኪ ሥራዎች ላይ ተሰማርቶ ይገኛል፡፡ ቤአኤካ ከፍተኛ ጥራት ያላቸው የተለያዩ ምርቶችን የሚያመርት ሲሆን በግንባታ ማሽነሪ ኪራይ እና ጥገና፣ በህትመት ሥራ አገልግሎት፣ ቡናን ወደ ውጭ መላክን ጨምሮ በተለያዩ የአገልግሎት ዘርፎች ተሰማርቷል፡፡ በተለያዩ ምርትና አገልግሎቶች ላይ አሻራውን በማሳረፍ ጠንካራ መሰረት እየጣለ የሚገኝ ድርጅት ነው፡፡ በድርጅቱ የምስረታና የአገልግሎት ሂደት በርካታ ደንበኞችን ያፈራና እውቅና ያገኘ ኩባንያ ሲሆን በበርካታ ዘርፎች ከተለያዩ ተቋማት እውቅናና ምስጋና ተችሮታል፡፡

ቤአኤካ እ.አ.አ በ2010 ዓ.ም. በግንባታ ዘርፍ የጀመረው የንግድ እንቅስቃሴ በአጭር አመታት ውስጥ ወደ ተለያዩ የንግድ ዘርፎች በማስፋፋት ዘርፈ ብዙ በሆኑ የንግድ ዘርፎች ላይ ተሰማርቶ ይገኛል፡፡ ኩባንያው “በ2030 በኢትዮጵያ ግንባር ቀደም የንግድ ድርጅት መሆን” የሚለውን ተቀዳሚ ራዕዩን ለማሳካት እየተንቀሳቀሰ ይገኛል።

በማምረት ዘርፍ በአሁኑ ወቅት በባህርዳር እንዲሁም በኦሮሚያ ሸገር ከተማ “ታጠቅ” ኢንዱስትሪያል ዞን አካባቢ በሚገኙ ፋብሪካዎቹ የተለያዩ አይነት ቀለም፣ እብነበረድ፣ ግራናይት፣ ቴራዞ ንጣፍ እና የምግብ ዘይት በማምረት እየሰራ ይገኛል፡፡ ከላይ ከተጠቀሱት በተጨማሪ በአዲስ አበባ ከፍተኛ አቅም ያለው የቀለም ማምረቻ ፋብሪካ ግንባታና ተከላ አጠናቀን በማምረት ላይ እንገኛለን፡፡ በድሬዳዋና ባህርዳር ከተሞችም በዓለም አቀፍ ደረጃ ታዋቂ ከሆነው የቻይና ሻክማን ኩባንያ ጋር በጥምረት የከባድ መኪና መገጣጠሚያ ለማቋቋም እየተሰራ ነው፡፡ 

ድርጅታችን ደረጃ-1 የግንባታ ተቋራጭ ሲሆን በአስፓልት እና ጠጠር መንገዶች፣ የባቡር ሀዲድ፣ ግድቦች፣ የኢንዱስትሪ ፓርኮች፣ የቤቶች ልማት ግንባታን ጨምሮ በሚያከናውናቸው ተግባራት የጠቅላላ ንግድ ስራን ከሚያከናውኑ መሰል ድርጅቶች በግንባር ቀደምትነት ከሚጠቀሱት አንዱ ለመሆን በቅቷል፡፡ 

ስፔሻሊቲ አረቢካ ቡና፣ የተለያዩ የቅመማ ቅመም፣ የቅባት እህልና የጥራጥሬ ሰብሎች፣ የማርና የፍራፍሬ ልማት ላይ በመሰማራት ዘመናዊ ቴክኖሎጂዎችንና አሰራሮችን በመጠቀም በሰፊው ይገኛል፡፡
ቤአኤካ ከጊዜ ወደ ጊዜ እያደገ የመጣውን የአገር ውስጥ የኃይል ፍላጎት ለማርካት የበኩሉን ሚና ለመጫወትም በቅርቡ ኮከብ ፔትሮ በሚል ስያሜ የነዳጅ ኩባንያ አቋቁሟል። በዚህ የንግድ ዘርፍም ፔትሮሊየም እና ተያያዥ ምርቶችን በማስመጣት እና በማከፋፈል ስራውን እያከናወነ ይገኛል፡፡
ድርጅታችን በአስመጪ እና ላኪ የንግድ ዘርፍ ላይም በሰፊው እየሰራ ሲሆን ዓለም አቀፍ ደረጃቸውን የጠበቁ የግንባታ ማሽነሪዎችን እና መለዋወጫዎችን በማስመጣት እና በማከፋፈል ላይ ይገኛል፡፡ ሻክማን ከተባለው ግዙፉ የቻይና የከባድ ተሽከርከሪ ማምረቻ ጋር ባደረግነው ስምምነት መሰረትም የተሽከርካሪዎቹን አካላት በማስመጣት በሀገር ውስጥ የመገጣጠም፣ የሽያጭና የጥገና እንዲሁም የመለዋወጫ አቅርቦት ሥራዎችን በማከናወን ይገኛል፡፡ በኤክስፖርት ዘርፍም ቤአኤካ በአውሮፓ፣ አሜሪካ፣ እስያ እና በመካከለኛው ምስራቅ ዋና ዋና የገበያ መዳረሻዎች ላይ ትኩረት በማድረግ ቡናና የቅባት እህሎችን ይልካል/በመላክ ላይ ይገኛል፡፡

ድርጅታችን በሚገባ የተደራጁና ዘመናዊ አገልግሎት የሚሰጡ የአገግልግሎት ዘርፎችም ያሉት ሲሆን ከነዚህም መካከል፡-

  • የከባድ ማሽነሪ ጥገና ወርክሾፕ
  • የግንባታ ማሽነሪዎች ኪራይ አገልግሎቶች
  • የቡና ማዘጋጃ፣ ማከማቻና ማቀነባበሪያና
  • የማተሚያ አገልግሎቶች ተጠቃሽ ናቸው፡፡
ቤአኤካ በአሁኑ ሰዓት በሁሉም ዘርፎቹ ቀዳሚ ሆኖ ለመገኘት የሚያደርገውን ጉዞ የሚያፋጥኑና በተለያዩ የሙያ ዘርፎችና የትምህርት ደረጃዎች ከ7 ሺ በላይ ለሚሆኑ ሰራተኞች የስራ ዕድል የፈጠረ ግዙፍ አገር በቀል ድርጅት ነው፡፡
amአማርኛ