ምርምር እና ቢዝነስ ዴቨሎፕመንት

ድርጅታችን ቤአኤካ ቀጣይ ዕድገቱና የረጅም ጊዜ ስኬቱ በምርምር እና ቢዝነስ ዴቨሎፕመንት ላይ የተመሰረተ እንደሆነ በእጅጉ ይገነዘባል። በሀገራችን ለጠቅላላ ንግድ ስራው የሚፈጠሩ ምቹ ሁኔታዎችን በአግባቡ ለመጠቀም እና ሊፈጠሩ የሚችሉ ተግዳሮቶችን በብቃት ለማለፍ ይችል ዘንድ ኩባንያው ራሱን የቻለ የቢዝነስ ዴቨሎፕመንት ዲፓርትመንት አቋቁሟል።

በዚህ የስራ ክፍል የቢዝነስ ጥናትና ምርምርን የማካሄድ፣ ድርጅታችን በጠራ ዕቅድ እንዲመራ፣ ድጋፍና ክትትል የማድረግ ኃላፊነቶችን ይወስዳል።

  • አዳዲስ አሰራሮችና ቴክኖሎጂዎችን መጠቀም
  • የኩባንያውን ነባር የሥራ ዘርፎች በጠንካራ አሰራር በማገዝ ውጤታማ እንዲሆኑ ማድረግና አዳዲስ የተሻሻሉ አሰራሮችን በማፈላለግ በድርጅቱ የተለያዩ ዘርፎች ጥቅም ላይ እንዲውሉ ማገዝ፣
  • አዳዲስ የንግድ መስመሮችን የቴክኒክ እና የፋይናንስ አዋጭነት ለመገምገም የአዋጭነት ጥናቶችን ማካሄድ።
  • የአዋጭነት ጥናቶችን ማካሄድና ከኩባንያው ስትራቴጂክ ዕቅድ ጋር የሚጣጣም ሁሉን አቀፍ እና የተቀናጀ የኮርፖሬት ፕላን ማዘጋጀት፣ አተገባበሩን በትጋት በመከታተልና በመቆጣጠር አጠቃላይ ውጤታማ የቢዝነስ የሥራ ክንውን በድርጅቱ እንዲኖር የበኩሉን ድርሻ ይወጣል።
  • ቤአኤካ ውስጥ ያለው እያንዳንዱ የንግድ ክፍል ከሁለቱም ሀገራዊ እና አለምአቀፋዊ ምርጥ ተሞክሮዎች ጋር በተጣጣመ ደረጃውን የጠበቀ አሰራርን የሚያከብር መሆኑን ማረጋገጥ።
  • በንግድ ጥናትና ምርምር ሥራወች ላይ በንቃት በመሳተፍ፣ በአዳዲስ ፈጠራወች ግንባር ቀደም ሆኖ ለመቆየት፣ ስልታዊ የንግድ ዕድሎችን ለመጠቀም እና በተለያዩ የንግድ ስራዎቹ ላይ ዘላቂ እድገትን ለማምጣት ያለመ አሰራርን በዚህ ክፍል ይተገብራል፡፡
amአማርኛ