+251-111-268019
customercare@beaeka.com
Elilta Bldg 4th floor
“በአማራጭና በታዳሽ ሀይል የሚሰሩ መኪኖችን ወደ ሀገር ማስገባት ቀዳሚ አጀንዳችን ነው!” የቤአኤካ ግሩፕ ማኔጂንግ ዳይሬክተር አቶ ሚካኤል ካሳ፡፡አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 17፣ 2018 (ቤአኤካ ሚዲያና ኮሙኒኬሽን)
ቤአኤካ ግሩፕ ከቻይናው የካባድ መኪና ቀዳሚ አምራች ከሆነው እና ከግዙፉ ሻክማን ኩባንያ ጋር አብሮ ለመስራት የሚያስችል ስምምነት ጥቅምት 11 ቀን /2018ዓ.ም በሸራተን አዲስ ሆቴል አድርገዋል፡፡
የቤአኤካ ግሩፕ ማኔጂንግ ዳይሬክተር አቶ ሚካኤል ካሳ ከስምምነቱ በኃላ ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ ድርጅቱ ኢትዮጵያ ውስጥ በአማራጭ ኃይል እንዲሁም በታዳሽ ኃይል የሚንቀሳቀሱ ከባድ ተሽከርካሪዎች ላይ ትኩረት እንደሚያደግ ገልፀው በቅርቡ በታዳሽ ሀይል የሚሰሩ 150 መኪኖች ወደ ሀገር ውስጥ እንደሚገቡም አክለዋል ::
በቻይና ሀገር የሚገኘው የሻክማን የመኪና አምራች ብቸኛ የኢትዮጵያ ወኪል የሆነው እና ከዚህ ቀደም የሻክማንን የደረቅ፣ የፈሳሽ እንዲሁም የኮንስትራክሽን ከባድ መኪኖችን ወደ ሀገራችን በማስመጣት የሚታወቀው ቤአኤካ በኢትዮጵያ በፈሳሽ የተፈጥሮ ጋዝ (LNG) እና በኤሌክትሪክ ኃይል የሚሠሩ (EV) የከባድ መኪኖች ለማስገባት መስማማታቸውን ገልፀው በአንድ አመት ውስጥ በመጀመሪያው ዙር ብቻ 1 ሺህ 500 መኪኖችን ገጣጥሞ ማቅረብ የሚያስችል ፋብሪካ ግንባታ በመጠናቀቅ ላይ ነው ብለዋል ::የሻንዥ አውቶሞቢል ግሩፕ(ሻክማን) ዋና ስራ አስኪያጅ ቻው ሽያንግሻንግ በበኩላቸው ካምፓኒያቸው ኢትዮጵያን ጨምሮ በሌሎች የአፍሪካ ሀገራት ከ30 አመት በላይ ምርት የማቅረብ ልምድ ያለው ሲሆን የአፍሪካ ገበያ ድርሻው ከድርጅቱ አመታዊ ሽያጭ ውስጥ 45 በመቶ እንደሚሸፍንም ገልፀዋል ::
ጥራት ያላቸው ምርቶችን በፍጥነት በማቅረብ በኢትዮጵያ ስራ ፈጠራ እና ሎጀስቲክስ አቅርቦት የበኩላቸውን እንደሚወጡ ገልፀዋል ::
በዚህ የሁለቱ የንግድ ድርጅቶች የስምምነት መድረክ ላይ የኢትዮ ቻይና የቢዝነስ ፎረም ጎን ለጎን የተካሄደ ሲሆን ከቻይና ሻንዥ ግዛት የመጡ ክ30 በላይ ከንግዱ ማህበረሰብ የተውጣጡ ግለሰቦችና የአካባቢው ባለስልጣናት ተገኝተዋል ::
በፎረሙ ላይ ላይ የተገኙት የኢንቨስትመት ኮሚሽን ኮሚሽነር ዘለቀ ተመስገን (ዶ/ር) በኢትዮጵያና የቻይና መካከል ለዘመናት የዘለቀው የንግድ፣ የቴክኖሎጂ ሽግግር፣ የባህል እና ሌሎች ግንኙነቶች በሁለቱ የንግድ ድርጅቶች ይበልጥ ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ ገልፀዋል ::
Your email address will not be published. Required fields are marked *