የቤአኤካ ጠቅላላ ንግድ ስራ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር ሰራተኞች በአንድ ጀምበር 500 ሚሊየን ችግኞችን የመትከል የአረንጓዴ አሻራ ሀገራዊ መርሀ ግብር ላይ ተሳትፎ አደረጉ።

  • Home
  • Uncategorized
  • የቤአኤካ ጠቅላላ ንግድ ስራ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር ሰራተኞች በአንድ ጀምበር 500 ሚሊየን ችግኞችን የመትከል የአረንጓዴ አሻራ ሀገራዊ መርሀ ግብር ላይ ተሳትፎ አደረጉ።

በቀን 500 ሚሊዮን ችግኞችን በመትከል በአረንጓዴው ሌጋሲ ሀገር አቀፍ መርሃ ግብር ተሳትፏል።


አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 10፣ 2015 (ቤአኤካ ሚዲያና ኮሙኒኬሽን)

የችግኝ ተከላው አዲስ አበባ ንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለከተማ ወረዳ 14 በድርጅቱ ፋብሪካ አካባቢ ተከናውኗል።

በመርሀ ግብሩ ተሳታፊ የነበሩ የድርጅቱ አመራሮችና ሰራተኞች በዚህ ችግኝ ተከላ በመገኘት ታሪካዊና ለትውልድ የሚሻገር አሻራ በማሳረፋቸው መደሰታቸውን ተናግረዋል።

የቤአኤካ ጠ/ንግድ ስራዎች ድርጅት ማኔጅንግ ዳይሬክተር አቶ ሚካኤል ካሳ ችግኞችን በመትከል ብቻ ሳይሆን ተንከባክቦ ጽድቀታቸውን በማረጋገጥ ሀገር የያዘችው የአረንጓዴ አሻራ መርሀ ግብር እንዲሳካ ቤአኤካ ተሳትፎውን አጠናክሮ እንደሚቀጥል አረጋግጠዋል።

ባለፉት አመታት ተተክለው ዛሬ ላይ የአካባቢውን ልምላሜ ያስጠበቁ የተለያዩ ዛፎችን በድርጅቱ ዙሪያ መመልከታችን የዚህ ቅርብ ማሳያ ነው ሲሉም ተናግረዋል።

ቤአኤካ ጠቅላላ ንግድ ስራዎች ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር ከሀገራዊ መርሀ ግብር ተሳትፎዎች ባሻገር ፕሮጀክቶቹ ባሉበት ቦታዎች የአካባቢን ስነ ምህዳር በሚያስጠብቁና በሌሎች የማህበረሰብ አገልግሎት ተግባራት ላይ በመሳተፍም ማህበራዊ ኃላፊነቱን እየተወጣ የሚገኝ ድርጅት መሆኑን አስታውሰዋል።

አስተያየት ይስጡ

Your email address will not be published. Required fields are marked *

amአማርኛ