ከውጭ የምናስመጣቸው ማሽነሪዎች አለማቀፍ ደረጃቸውን የጠበቁ፣ ዘመናዊና አቅም ያላቸውን መሳሪያዎች ለሚፈልጉ የንግድ ዘርፎች ሁሉ ተመራጭ ናቸው፡፡ በኢንዱስትሪውና በደንበኞቻችን ፍላጐት መሰረት የምናስመጣቸው መሳሪያና ማሽነሪዎች በቅልጥፍናና ተጠቃሚዎቻችን በሚፈልጉት መሰረት በመሆኑ ከደንበኝነታችን ጋር ያለን ግኑኝነት እንዲጠናክር አድርጐልናል፡፡
ቤአኤካ የተሟላ አገልግሎት መስጠት የሚችል የተሽከርካሪ ጥገና ወርክሾፕ ያለው ሲሆን አሜሪካ፣ አውሮፓና ጃፓን ሰራሽ መኪኖችን ለመጠገን ሙሉ አቅም ያለው ግዙፍ ማዕከል ነው፡፡ በኢንሹራንስ ድርጅቶችና በሌሎች ተቋማት የሚመረጠው ጋራዣችን የመኪና ቀለም ቅብ፣ የተሽከርካሪ ኮምፒዩተር ሲስተም ጥገና፣ መካኒካልና ኤሌክትሪካል ስራዎችና ሌሎችንም በጥራትና በቅልጥፍና የሚሰራ ሲሆን በዘመናዊ የጥገና መሳሪያዎችና ግብአቶችም የተሟላ ነው፡፡
ድርጅታችን በዓለም ታዋቂ ብራንድ ያላቸውን ብቁ የግንባታ ማሽነሪዎችንና ተሽከርካሪዎችን ለኪራይ ያቀርባል፡፡
አገልግሎታችንን የበለጠ ፈጣን እና አስተማማኝ ለማድረግም ተንቀሳቃሽ የጥገና አገልግሎት በመስጠት በምንፈለግበት ቦታ ሁሉ ፈጥነን እንደርሳለን፡፡ ይህም ደንበኞቻችን በአጭር ጊዜ በተከራዩት ማሽነሪዎች ቀልጣፋ አገልግሎት እንዲሰጡና ውጤታማ እንዲሆኑ ያስችላቸዋል፡፡