የውስጥ ኦዲት አገልግሎትን ዘመናዊ፣ ሙያዊ፣ በዓለም አቀፍ የውስጥ ኦዲተሮች ማኅበር መርሆች ላይ የተመሰረተ የለውጥ ጉዞ ማስጀመርን ዓላማ ያደረገ ሥልጠና ተሰጠ፡፡

  • መነሻ
  • Uncategorized
  • የውስጥ ኦዲት አገልግሎትን ዘመናዊ፣ ሙያዊ፣ በዓለም አቀፍ የውስጥ ኦዲተሮች ማኅበር መርሆች ላይ የተመሰረተ የለውጥ ጉዞ ማስጀመርን ዓላማ ያደረገ ሥልጠና ተሰጠ፡፡

የውስጥ ኦዲት አገልግሎትን ዘመናዊ፣ ሙያዊ፣ በዓለም አቀፍ የውስጥ ኦዲተሮች ማኅበር መርሆች ላይ የተመሰረተ የለውጥ ጉዞ ማስጀመርን ዓላማ ያደረገ ሥልጠና ተሰጠ፡፡
አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 28/2017 (ቤአኤካ ሚዲያና ኮሙኒኬሽን)

ለቤአኤካ ጠቅላላ ንግድ ሥራ ኃላ/ የተ/ የግ/ማኅበር የውስጥ ኦዲተሮች ስልጠና ተሰጥቷል፡፡

በሥልጠናው መክፈቻ ላይ የተገኙት የድርጅቱ የኦፕሬሽን ዘርፍ ም/ማኔጅንግ ዳይሬክተር አቶ ወንድይፍራው ጌታቸው ከድርጅቱ ስፋት፣ አዳዲስ ትግበራዎች፣ ቴክኖሎጂያዊ ለውጦች እንዲሁም በፍጥነት እየተለወጠ ካለው ዓለም አቀፋዊ ሁኔታ ጋር ራስን ማብቃት የሚያስፈልግ በመሆኑ ሥልጠናው ቁልፍ ሚና ይጫወታል ብለዋል፡፡

ሥልጠናው የውስጥ ኦዲት የለውጥ ጉዞን የተመለከቱ ይዘቶችን ያካተተ፣ ከተበታተኑ አሰራሮች መውጣት የሚያስችል፣ የሙያ ክህሎቶችን የሚያሳድግ፣ የውስጥ ኦዲት ክፍል ለድርጅቱ እሴት የሚፈጥርና ታማኝ አማካሪ እንዲሆን ጠንካራ መሰረት ይጥላል ያሉት ደግሞ የውስጥ ኦዲት አገልግሎት ኃላፊ የሆኑት አቶ ኢንሰርሙ ገ/ጊዮርጊስ ናቸው፡፡

ሥልጠናው አዲሱ የገቢ ግብር አዋጅ ድንጋጌ በኦዲት ሥራ ላይ ሊኖረው የሚችለውን ተፅዕኖ በመመልከት በሥራው የሚያጋጥሙ የሥነ-ምግባር ጥያቄዎችን በደንቡ መሰረት ለመመለስ አቅም እንደሚፈጥርም ታምኖበታል፡፡

የኦዲት ተግባራትን ከድርጅቱ ስትራቴጅካዊ ግቦች ጋር በማጣጣም ለማከናወን ያስችላል ያሉት አቶ ኢንሰርሙ የውስጥ ኦዲት አገልግሎትን ዘመናዊ፣ ሙያዊ፣ በዓለም አቀፍ የውስጥ ኦዲተሮች ማኅበር መርሆች ላይ የተመሰረተ የለውጥ ጉዞ ማስጀመርን ዓላማው አድርጎ የተሰጠ ሥልጠና መሆኑን አንስተዋል፡፡

ነሐሴ 26 እና 27/2017 ዓ.ም. ለ2 ቀናት በተሰጠው ሥልጠና የዋናው መ/ቤት እና የፕሮጀክቶች የውስጥ ኦዲት ክፍል ኃላፊዎችና ባለሙያዎች ተሳትፈውበታል፡፡

Leave A Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

en_USEnglish