+251-111-268019
customercare@beaeka.com
Elilta Bldg 4th floor
የኢትዮጵያ የመሰረተ ልማት እና ኮንስትራክሽን ሳምንት ከሚያዝያ 9-11/2018 ዓ.ም ድረስ “ኢትዮጵያ ትገነባለች፤ ፈጠራ፣ ፍጥነት እና ጥራት ለመሰረተ ልማት እመርታ” በሚል መሪ ሐሳብ በፓናል ውይይትና ኤግዚቢሽን በአዲስ ኢንተርናሽናል ኮንቬንሽን ማዕከል ተካሂዷል።
ድርጅታችን ቤአኤካ ጠቅላላ ንግድ ሥራ ኃላ/ የተ/ የግ/ ማኅበር በዚህ ኤግዚቢሽን ላይ ከኮንስትራክሽን ሥራዎች ጋር ተያያዥነት ያላቸውን ምርትና አገልግሎቶች ለእይታ ይዞ ቀርቧል፡፡
በዚሁ ፕሮግራም ላይ ድርጅታችን በኮንስትራክሽን ዘርፍ ላበረከተው አስተዋጽኦ ምርጥ የዘርፉ ፈፃሚወች ተብለው ከተለዩ የመጀመሪያዎቹ 10 ኮንትራክተሮች አንዱ ሆኖ ለሽልማት በቅቷል፡፡
የ2024/25 የዘርፉ ተሸላሚ በመሆናችን ለመላው የድርጅታችን ሠራተኞችና የቤአኤካ ቤተሰቦች እንኳን ደስ አለን፤ ደስ አላችሁ እንላለን፡፡
ድርጅታችን የሚታወቅበትን ጥራትና ቅልጥፍና በከፍታ በመተግበር የደንበኞቻችን ኩራት ሆነን እንቀጥላለን!!
Your email address will not be published. Required fields are marked *