ድርጅታችን ቤአኤካ ጠቅላላ የንግድ ስራ ድርጅት  በባህር ዳር ከተማ  “ፈለገ ግዮን ” የተሰኘ ዘመናዊ ሪዞርት  አስመረቀ:: ሚያዝያ 25 ፣ 2018 ዓ.ም (ቤአኤካ ሚዲያና ኮሙኒኬሽን)

  • መነሻ
  • Uncategorized
  • ድርጅታችን ቤአኤካ ጠቅላላ የንግድ ስራ ድርጅት  በባህር ዳር ከተማ  “ፈለገ ግዮን ” የተሰኘ ዘመናዊ ሪዞርት  አስመረቀ:: ሚያዝያ 25 ፣ 2018 ዓ.ም (ቤአኤካ ሚዲያና ኮሙኒኬሽን)

እንኳን ደስ አላችሁ፤ እንኳን ደስ አለን!

ድርጅታችን ቤአኤካ ጠቅላላ የንግድ ስራ ድርጅት  በባህር ዳር ከተማ  “ፈለገ ግዮን ” የተሰኘ ዘመናዊ ሪዞርት  አስመረቀ::

ሚያዝያ 25 ፣ 2018 ዓ.ም (ቤአኤካ ሚዲያና ኮሙኒኬሽን)

በዚህ የምረቃ ስነ ስርዓት ላይ የድርጅታችን መስራችና ዋና ሥራ አስፈፃሚ ባለራዕይ አቶ ካሳሁን ምስጋናው ችግር የማይበግራቸው የልማት አርበኛ ተብለው በፌደራልና በክልል ከፍተኛ አመራሮች ከ ቤተሰቦቻቸው  ጋር እውቅና ተሰጥቷቸዋል  ::

ይህ ግዙፍ የቱሪዝም መዳረሻ  በ4.5 ቢሊዮን ብር ወጪ የተገነባ ሲሆን ግንባታውም በጥራትና በፈጣን ሁኔታ በሁለት ዓመት ከስድስት ወራት ጊዜ ውስጥ ተጠናቆ ለምረቃ በቅቷል።

የቱሪዝም ዘርፉን በግሉ ዘርፍ ለማጠናከር “ልባችን ኢትዮጵያ ደረጃችን ዓለም አቀፍ!” በሚል መሪ ቃል በድርጅታችን ሥር “ሮዳ ሆስፒታሊቲ ግሩፕ” መቋቋሙ የተበሰረ ሲሆን ግሩፑ አዲሱን ፈለገ ግዮን ሪዞርት እና የጎርጎራ ኢኮ ሪዞርትን በአንድነት በማስተዳደር ዘመናዊና ተወዳዳሪ አገልግሎት መስጠት እንደሚጀምር በመታወቁ የተሰማንን ደስታ እንገልፃለን።

Leave A Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

en_USEnglish