በድርጅታችን ተቋራጭነት ሲከናወን የቆየው የመገጭ ግድብ ግንባታ ለምረቃ በቅቷል፡

  • መነሻ
  • Uncategorized
  • በድርጅታችን ተቋራጭነት ሲከናወን የቆየው የመገጭ ግድብ ግንባታ ለምረቃ በቅቷል፡

በድርጅታችን ተቋራጭነት ሲከናወን የቆየው የመገጭ ግድብ ግንባታ ለምረቃ በቅቷል፡፡
ጎንደር፣ ጥቅምት 13፣ 2019 (ቤአኤካ የኮርፖሬት ጉዳዮችና ኮሙኒኬሽን)
   ለታሪካዊቷ ጎንደር እና ለአካባቢዋ ማህበረሰብ ትልቅ የምስራች የሆነውን የመገጭ መስኖ ግድብ ፕሮጀክት በይፋ ተመርቋል፡፡
    በምረቃው ወቅት የተገኙት የኢፌዲሪ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ (ዶ/ር) ይህ ፕሮጀክት ረጅም ዓመታት የዕቅድና አተገባበር መጓተት ቢፈታተነውም፣ በመደመር እሳቤ የአፈጻጸም ችግሮቹን በመፍታት ወደ ታላቅ በረከት መለወጥ ችለናል ብለዋል፡፡
   ይህ ግድብ 185 ሚሊዮን ሜትር ኩብ ውሃ የመያዝ አቅም ያለውና ከ17 ሺህ ሄክታር በላይ መሬትን በመስኖ በማልማት በአካባቢው የሚኖሩ በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ አርሶ አደሮችን በቀጥታ ተጠቃሚ በማድረግ የአካባቢውን ነዋሪዎች የልማት ጥያቄ በዘላቂነት መመለስ የሚያስችል ታላቅ ፕሮጀክት ነው።
  ግድቡ ለጎንደር ከተማና በዙሪያዋ ላሉ ከተሞች አስተማማኝ ንፁህ የመጠጥ ውሃ ከማቅረብ ባለፈ፣  ሁለንተናዊ የኢኮኖሚ መነቃቃትን ይዞ የመጣ ነው። በግድቡ ሰው-ሰራሽ ሀይቅ ዙሪያ የሚስፋፉት የከተማ ግብርና፣ መጠነ-ሰፊ የአሳ እርባታ፣ እንዲሁም ለቱሪዝም ልማት የሚሆኑ የመዝናኛ ሪዞርቶች እና ሎጆች ለአካባቢው ወጣቶች ሰፊ የስራ ዕድል የሚፈጥሩና የንግድ እንቅስቃሴውን የሚያሳድጉ ናቸው።
   ይህን ስኬት ለእይታ ለማብቃት በጥብቅ ክትትልና ድጋፍ እውን ማድረግ የቻልን ቢሆንም፣ ጎንደር ገና ብዙ ሊሰራላት የሚገባ ከተማ እንደመሆኗ ህዝቡ በልማቱ ላይ በንቃት እንዲሳተፍ ጥሪዬን አቀርባለሁ ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ የኢትዮጵያ እድገት ሁሉንም አካባቢዎች ያካተተና ሁሉንም ዜጋ እኩል የሚያቅፍ እንዲሆን በትጋት መስራታችንን እንቀጥላለን ሲሉ አረጋግጠዋል፡፡
  ቤአኤካ ጠቅላላ ንግድ ሥራ የመገጭ ግድብ ፕሮጀክቱን ከተረከበበት ጊዜ አንስቶ በተያዘለት ጊዜ እንዲጠናቀቅ ላደረገው ጥረት የድርጅታችን መስራች አቶ ካሳሁን ምስጋናውና ድርጅታችን ቤአኤካ ምስጋና ተችሮታል፡፡
   ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ ጎርጎራ ኢኮ ሪዞርትንና ባህርዳር ፈለገ ጊዮን ኢኮ ሪዞርትን በጥራትና በፍጥነት በመገንባት፣ የፋሲል አብያተ መንግስታት ግቢ እድሳትን ጥራትና ታሪካዊነቱን ጠብቆ በማከናወን ያላሳፈሩን አቶ ካሳሁን ምስጋናው በመገጭ ግድብም ይህንኑ ደግመውታል ሲሉ አሞግሰዋቸዋል፡፡
    ጠቅላይ ሚኒስትሩ አክለውም አቶ ካሳሁንና ድርጅታቸው በመገጭ ግድብ ዙሪያ ደረጃውን የጠበቀ ሎጅ ገንብተውልን በሚቀጥለው አመት ለጉብኝት በዚህ ስፍራ ስንመጣ ግንባታውን እንደሚያጠናቅቁ፣ ለዚህም ከክልሉ መንግስት፣ ከከተማ አስተዳደሩና ከማህበረሰቡ ድጋፍ እንደሚያገኙ እምነቴ ነው ብለዋል፡፡

Leave A Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

en_USEnglish