+251-111-268019
customercare@beaeka.com
Elilta Bldg 4th floor
የቤአኤካ ጠቅላላ ንግድ ሥራ ኃላ/ የተ/ የግ/ ማኅበር ሠራተኞች የደም ልገሳ አከናወኑ፡፡
አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 28/2017 (ቤአኤካ ሚዲያና ኮሙኒኬሽን)
የደም ልገሳ መርሃ ግብሩ ላይ የድርጅቱ የዋናው መ/ቤት ሠራተኞች የተሳተፉበት ሲሆን በፕሮግራሙ ላይ የድርጅቱ የሀብት አስተዳደር ም/ማኔጅንግ ዳይሬክተር አቶ ምስጋናው ዘውዴ ተገኝተው መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡
ቤአኤካ ከደመበኛ ሥራው በተጨማሪ የማህበረሰብ አገልግሎትና የበጎ ፈቃድ ተግባራትን ቁልፍ ጉዳይ አድርጎ እያከናወነ ስለመሆኑ ተናግረዋል፡፡
በአካባቢ ጥበቃ የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር፣ ከዚህ በፊት የተደረጉ የደም ልገሳዎችና ሌሎች የበጎ ፈቃድ ተግባራትን ያስታወሱት ም/ማኔጅንግ ዳይሬክተሩ ይህ የደም ልገሳም ሌላው ማሳያ ስለመሆኑ፣ በቀጣይ ጊዜያትም የደም ልገሳና ሌሎች የበጎ ፈቃድ ተግባራት ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ በመግለጽ በተግባሩ የተሳተፉ ደም ለጋሾችና ፕሮግራሙን ላስተባበሩ አካላት ምስጋናቸውን ችረዋል፡፡
በደም ልገሳ መርሃ ግብሩ ተሳታፊ የነበሩ ሠራተኞች በዚህ በጎ ተግባር ላይ መሳተፋቸውና ክቡር የሆነውን የሰው ልጅ ሕይወት ለማትረፍ የሚደረገው አስተዋጽኦ አካል መሆናቸው እንዳስደሰታቸው ተናግረዋል፡፡
የደም ባንክ አስተባባሪዋ ሳራ ወልዴም በተለያዩ ምክንያቶች ሕይወታቸውን ለሚያጡ ወገኖች ለመድረስ የዚህ አይነቱ የተቋማት የደም ልገሳ መርሃ ግብር የሚበረታታ መሆኑን አንስተዋል፡፡
የቤአኤካ ሠራተኞች 5ቱን የጳጉሜ ቀናትም የተለያዩ የበጎ አድራጎት ተግባራትን በማከናወንና እርስ በርስ ትስስርን የሚያጠናክሩ ፕሮግራሞችን በማዘጋጀት መጪውን አዲስ ዓመት ይቀበላሉ፡፡
Your email address will not be published. Required fields are marked *