+251-111-268019
customercare@beaeka.com
Elilta Bldg 4th floor
የቤአኤካ ጠቅላላ ንግድ ሥራ ኃላ/ የተ/ የግ/ ማኅበር የመምሪያ ዳይሬክተሮችና የሥራ ክፍል ኃላፊዎች በተገኙበት የ2017 በጀት ዓመት ዕቅድ አፈፃፀምና የ2018 ዓ.ም. በጀት ዓመት ዕቅድ ውይይት ተካሂዷል፡፡
የድርጅቱ ማኔጅንግ ዳይሬክተር አቶ ሚካኤል ካሳ እና የኦፕሬሽን ዘርፍ ም/ማኔጅንግ ዳይሬክተር አቶ ወንድይፍራው ጌታቸው በሪሰርችና ቢዝነስ ዴቨሎፕመንት መምሪያ የቀረበውን ዕቅድና ሪፖርት መሰረት አድርገው ውይይቱን መርተዋል፡፡
በ2017 በጀት ዓመት የተገኙ ውጤቶች፣ ያጋጠሙ ችግሮችና የመፍትሄ አቅጣጫዎች እንዲሁም የ2018 ዓ.ም. ቁልፍ የትኩረት ጉዳዮች ቀርበው ውይይት ተደርጎባቸዋል፡፡
ማኔጅንግ ዳይሬክተሩ አቶ ሚካኤል ካሳ በ2018 በጀት ዓመት ድርጅቱ በሁሉም ዘርፍ የሚያደርገውን ግስጋሴ ለማስቀጠል ሁሉም መምሪያዎች ውጤት ላይ ያተኮረ ጥረት እንዲያደርጉ አሳስበዋል፡፡
***********
Your email address will not be published. Required fields are marked *