አለማቀፍ የሴቶች ቀን (ማርች-8) በቤአኤካ ጠቅላላ የግድ ሥራ ኃላ/ የተ/ የግ ማኅበር ተከበረ:: አዲስ አበባ፣ የካቲት 28፣ 2018 (ቤአኤካ ሚዲያና ኮሙኒኬሽን)

  • መነሻ
  • Uncategorized
  • አለማቀፍ የሴቶች ቀን (ማርች-8) በቤአኤካ ጠቅላላ የግድ ሥራ ኃላ/ የተ/ የግ ማኅበር ተከበረ:: አዲስ አበባ፣ የካቲት 28፣ 2018 (ቤአኤካ ሚዲያና ኮሙኒኬሽን)

አለማቀፍ የሴቶች ቀን (ማርች-8) በቤአኤካ ጠቅላላ የግድ ሥራ ኃላ/ የተ/ የግ ማኅበር ተከበረ:: አዲስ አበባ፣ የካቲት 28፣ 2018 (ቤአኤካ ሚዲያና ኮሙኒኬሽን)

የቤአኤካ ጠቅላላ ንግድ ሥራ ኃላ/ የተ/ የግ/ ማኀበር ዋናው መ/ቤት ሴት ሠራተኞች ማርች-8 አለማቀፍ የሴቶች ቀንን አክብረዋል። በክብረ-በዓሉ ተገኝተው የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የድርጅቱ የሀብት አስተዳደር ም/ማኔጅንግ ዳይሬክተር አቶ ምስጋናው ዘውዴ ሴቶች በሁለንተናዊ ዘርፎች የማይተካ አስተዋፅኦ እያበረከቱ ነው ያሉ ሲሆን በተለይ ትውልድ ማስቀጠል፣ ከቤተሰብ መምራት፣ ማህበረሰብን መገንባት እንዲሁም የሀገር ዕድገት ያለ ሴቶች ንቁ ተሳትፎ የማይታሰብ ነው ብለዋል፡፡ ዛሬ ዛሬ ከሀገር አልፎ በአለማቀፍ ደረጃ ወሳኝ ለውጦች እየመጡ ያሉት በጠንካራ በሴቶች ተሳትፎ መሆኑን የጠቀሱት አቶ ምስጋናው እዚህ ድርጅት ውስጥ ያሉ ሴቶችም ለዚሁ ምስክር መሆናቸውን ተናግረዋል፡፡ በድርጅታችን ስኬቶች ሁሉ ሴቶች ለነበራቸው ተሳትፎ ምስጋና ያቀረቡት ም/ማኔጅንግ ዳይሬክተሩ ሴቶችን ይበልጥ በማብቃት ለተሻለ ውጤት መትጋት እንደሚገባ አጽንኦት ሰጥተዋል፡፡ የቤአኤካ ጠቅላላ ንግድ ሥራ ኃላ/ የተ/ የግ/ ማህበር የህግ ባለሙያ ሊዲያ ዋሪ በበኩሏ “የሴቶች ድምፅ ለእኩልነትና ለበለፀገች ኢትዮጵያ” በሚል መሪ ቃል አለም አቀፍ የሴቶች ቀን /ማርች-8/ በዓለም አቀፍ ደረጃ ለ115ኛ ጊዜ፣ በኢትዮጵያ ደረጃ ለ50ኛ ጊዜ ዛሬ በድርጅታችን ስናከብር የሴቶችን መብት በማስጠበቅና ሁለንተናዊ ተጠቃሚነትን በማረጋገጥ ነው ብላለች::

Leave A Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

en_USEnglish